Bishop Profile

የብፁዕ አቡነ ልሳነ-ክርስቶስ ማቴዎስ አጭር የሕይወት ታሪክ ልደት፣ልጅነትና ዕድገት

ብፁዕ አቡነ ልሳነክርስቶስ ማቴዎስ ካቶሊክ ከሆኑት ወላጆቻቸው ከአባታቸው ከአቶ ማቴዎስ ሰማሁን እና ከእናቻቸው ከወ/ሮ አየለች ቸርነት ታህሣሥ 1ዐ/1952ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ተወለዱ፡፡ በወላጆቻቸውና በቁምስና ቤተክርስቲያናቸው /ልደተ ማርያም ካቶሊክ ቤተክርስቲያን/ የቅርብ ክትትልና ክርስቲያናዊ እንክብካቤ እያገኙ ያደጉት ብፁዕ አቡነ ልሳነክርስቶስ ምስጢረ ጥምቀት፣ ምስጢረ ቁርባንና ምስጢረ ሜሮን በልደታ ለማርያም ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ተቀብለዋል፡፡  ዕድሜያቸው ለትምህርት እንደደረሰም የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በላዛሪስት ካቶሊክ ት/ቤት እና በአሰረ ሐዋርያት ት/ቤት እንዲሁም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በመድሃኔ ዓለም አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አጠናቀዋል፡፡በወጣትነታቸው በቁምስናቸው በልደታ ለማርያም ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ንቁ ተሣትፎ የነበራቸው ሲሆን በቁምስናው ወጣት መዘምራን ማህበር ለረጅም ጊዜ በመዝሙር፣ በሙዚቃ መሣሪያ መጫወትና በማህበሩ አመራር ጉልህ አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡

የክህነት ጥሪ ምላሽ ዓብይ ዘርዓ ክህነት

ብፁዕ አቡነ ልሳነ ክርስቶስ ማቴዎስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ፣ በ1974ዓ.ም ለመንፈሳዊ ጥሪአቸው ምላሽ ለመስጠት የቅዱስ ኤፍሬም ካቶሊክ ዘርዓ ክህነት ተቀላቀሉ፡፡ ከዚያም ከ1974-198ዐ በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሕግና ደንብ መሠረት ለዲቁናና ለማዕረገ ክህነት የሚያበቃቸውን የስድስት ዓመት የፍልስፍናና ነገረ መለኮት ትምህርት በፍራንሲስካውያን የፍልስፍና የነገረ-መለኮት ተቋም ውስጥ በመንፈሳውያን አባቶች የቅርብ ክትትል ካጠናቀቁ በኋላ፡- በ198ዐዓ.ም ማዕረገ ዲቁናን በልደተ ማርያም ካቶሊክ ካቴድራል በብፁዕ ካርዲናል ጳውሎስ ፃድዋ እጅ ተቀብለዋል፡፡ ሚያዝያ 3ዐ ቀን 198ዐዓ.ም ማዕረ ክህነት በልደተ ማርያም ካቶሊክ ካቶድራል በብፁዕ ካርዲናል ጳውሎስ ፃድዋ እጅ ተቀብለዋል፡፡

የድኀረ ምረቃ ትምህርት

ከ1988-1992ዓ.ም በጣሊያን አገር ሮም ከተማ ውስጥ በሚገኘው የቅዱስ ቶማስ አኳይናስ ወይም አንጄሊኩም በሚባል ዩኒቨርስቲ በነገረ-መለኮት በተለይ በመንፈሳዊነት የላይሰንስ (License) ዲግሪ ተመርቀዋል፡፡ በተጨማሪም በኬንያ ናይሮቢ ውስጥ በሚገኘው (CUEA/ በተሰኘው ዩኒቨርስቲ በቤተክርስቲያን አመራር ሠርቲፊኬት አግኝተዋል፡፡

ሐዋርያዊ አገልግሎት

ማዕረገ ክህነት ከተቀበሉ በኋላ ሐዋርያዊ አገልግሎት የሰጡባቸው የአገልግሎት ዘርፎች ዝርዝር፡- ከሐምሌ 198ዐ – መስከረም 1988ዓ.ም ድረስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ካቶሊክ ወጣቶች መሪ ካህን፣ በተጨማሪም ከ1981 -1988ዓ.ም ድረስ የካቶሊክ መንፈሳዊ ተሃድሶ (Charismatic Movement) እንቅስቃሴ መሪ ካህን፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ወጣቶች ካቶሊካውያን ሠራተኞች እንቅስቃሴ መሥራችና መሪ ካህን፣

ከ1993 እስከ ህዳር 2ዐዐ1ዓ.ም ድረስ የአዲስ አበባ ሰበካ ካቶሊካውያን ምዕመናን ምክር ቤት መሪ ካህን::

ከ1993 – 1994ዓ.ም ድረስ የአዲስ አበባ ሰበካ ካቶሊክ ጠቅላይ   ጽ/ቤት ተጠባባቂ ዋና ጸሐፊና  ከ1994-1996ዓ.ም ድረስ የአዲስ አበባ ካቶሊካዊ ሰበካ ጠቅላይ ጽ/ቤት ተጠባባቂ ጠ/ጸሐፊና የሐዋርያዊ ጽ/ቤት ኃላፊ ከ1996-ጥር 22/2ዐዐ2ዓ.ም ድረስ የአዲስ አበባ ካቶሊካዊ ሰበካ ጠቅላይ ዋና ጸሐፊ ከጥቅምት 2ዐዐዐዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥር 22/2ዐዐ2ዓ.ም ድረስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ተጠባባቂ እንደራሴ በመሆን አገልግለዋል፡፡

d

ከአዲስ አበባ ካቶሊካዊ ሰበካ ጠቅላይ ጽህ ፈት ቤት ሰራተኞች  ጋር

ቅብዐተ ጵጵስናና ኃላፊነት

ቅዱስ አባታችን ቤኒዲክቶስ 16ኛ ክቡር አባ ልሳነ ክርስቶስ ማቴዎስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ረዳት ጳጳስና በተለይ የባሕርዳር አካባቢ ሐዋርያዊ ክልል ኃላፊ ሆነው እንዲያገለግሉ፣ እንዲሁም በሰሜን አፍሪካ ለምትገኘው ኑሚዲያ ማታር ገዳም የክብር ጳጳስ እንዲሆኑ ታህሣሥ 27 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም ሾመዋቸዋል፡፡ የቅብዐተ ጵጵስናቸው ስነ-ሥርዓት በብፁዕ አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካውያን መሪነት ሚያዝያ 1ዐ ቀን 2ዐዐ2ዓ.ም ከጠዋቱ 1፡3ዐ ጀምሮ በአዲስ አበባ ልደተ ማርያም ካቶሊክ ካቴድራል ተፈፅሟል፡፡

ቅብዐተ ጵጵስና ከተቀበሉ በኋላ በቤተክርስቲያን በተለይም በአዲስ አበባ ሀገረስብከት በተለያዩ የቤተክርስቲያን ኃላፊነት አገልግሎታቸውን ሰጥተዋል፡፡ እነዚህም፡

የአዲስ አበባ ሀገረስብከት ረዳት ጳጳስ ሆነው በተጨማሪ

የአዲስ አበባ ሀገረስብከት ጠቅላይ እንደራሴ (Vicar General)

የባህር ዳር ሐዋርያዊ ክልል ኃላፊ እና የአዲስ አበባ ካቶሊካዊ ሰበካ ጠቅላይ ጽ/ቤት አስተዳደር ቦርድ ሰበሳቢ ሆነው አገልግለዋል፡፡

በውጭ አገር በሚኖሩ ካቶሊካውያን የሚሰጠውን ሐዋርያዊ አገልግሎት በኃላፊነት በማስተማበር ሰርተዋል

ብፁዕ አቡነ ልሳነ ክርስቶስ ማቴዎስ የነፍሳት እረኛ ሆነው እንዲያገለግሉ በተሰየሙበት በባህርዳር-ደሴ ሀገረስብከት የሚሰጡትን ሐዋርያዊ አገልግሎት እግዚአብሔር አምላካችን እንዲባርክላቸው፣ ጸጋና በረከቱን እንዲያበዛላቸው፣ ረጅም ዕድሜና ጤና እንዲሰጣቸው እንለምናለን፡፡

ስለ ሁሉም ነገር ክብርና ምስጋና ለእግዚአብሔር ይሁን !

From July 1888G.C to Sep. 1996G.C served as Chaplain for the Archdiocesan Catholic youth and at the same time from 1989 to 1996 September he served as Chaplain of the Catholic Charismatic Movement and initiated and became the first Chaplain of Young Catholic Workers Movement of Ethiopia.

From August 2000 to October 2008 he served as:

Pastoral Coordinator of the Archdiocesan Catholic Secretariat (ACS). Chaplain of the Lay Apostolate Council of the Archdiocese of Addis Ababa. From 2001 -2003 Acting Secretary General of ACS

From 2003 up to January 2010 Secretary General of the

Archdiocesan Catholic Secretariat (ACS)

From 2008 August on wards served as Chaplain of Young Catholic Workers Movement of the Archdiocese of Addis Ababa.

On top of the above responsibilities since October 2008, he has served as an Acting Vicar General of the Archdiocese of Addis Ababa.

Episcopal Ordination

His Holiness pope Benedict XVI appointed Abba Lessanu Christos Matheos as Auxiliary Bishop of the Archdiocese of Addis Ababa and  with a particular responsibility for BahirDar Pastoral Territory.

His  Episcopal ordination  took place on April 18, 2010 at the Nativity Catholic Cathedral Church in Addis Ababa.Following his Episcopal ordination, in addition to his responsibility as Auxiliary Bishop & Bahir Dar pastoral Territory, he has served as Vicar General of the Archdiocese of Addis Ababa, and Board Chairman of the Archdiocesan Catholic Secretariat (ACS).

የእግዚአብሔር አገልጋዮች አገልጋይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘላለማዊ መታሰቢያ

ቤተክርስቲያን ለምዕመናን የምታበረክተው አገልግሎት ፍሬአማነት ሁላችንንም የሚያሳስበን ዐብይ ጉዳይ ነው፡፡ በኢትዮጵያ በምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቆዳ ስፋት ከፍተኛ በመሆኑ ለምዕመናን የምናበረክተውን አገልግሎት ተደራሽነት ለማስፋት አንዳንድ የሀገረ ስብከቱን ክልሎች እንደ አንድ ሰበካ ማቋቋም ትልቅ ሐዋርያዊ ፋይዳ ያለው ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ የመንጋው እረኛ የምዕመናንን አገልግሎት ከፍ ወዳለው ደረጃ ለማድረስ ካለው ጥልቅ ሐዋርያዊ ፍላጐት የተነሳ ከዚህ የሚከተለውን ሐዋርያዊ ድንጋጌ ያስተላልፋል፡፡ ለምዕመናን ነፍስ የምናበረክተውን አገልግሎት የተሻለ ለማድረግ የቅዱስ ጴጥሮስ ተተኪ የኩሏዊቷ ቤተክርስቲያን አባት በሰጡት ሐዋርያዊ ትዕዛዝ እና የምሥራቅ አብያተ ክርሲያናት ጉባኤ ሰብሳቢ የሆኑት ካርዲናል ባቀረቡት ሐዋርያዊ ምክር በመመራት ቤተ ክርስቲያን በሰጠችን ሐዋርያዊ ስልጣን መሠረት የባህር ዳር ደሴ ሀገረስብከትን መመሥረት አውጃለሁ፡፡

ይህ የባህር ዳር ደሴ ሀገረስብከት ተብሎ የሚጠራው ሰበካ በምሥራቅ ቤተክርስቲያን ሕገ ቀኖና መሠረት መብቶችን እና ግዴታዎችን አጠቃልሎ የያዘ ራሱን የቻለ ጳጳስ ያለው ሰበካ ነው፡፡ በዚህ መሠረት በባህር ዳር ደሴ ከተማ የሚቆመው ካቶድራል በመንበረ ጳጳስ ሆኖ መጠርያው ለ ‹እግዚአብሔር አብ› የተሰጠ ነው፡፡ ለዚሁ አዲስ ሰበካ ጠባቂ እና ባልደረባ ይሆን ዘንድ ቅዱስ ፍሬሚናጦስ አባ ከሳቴ ብርኅንን መርጠናል፡፡

አዲሱ የባህር ዳር ደሴ ሀገረስብከት በውስጡ Zስት ክፍሎችን የያዘ ሲሆን እነዚህም ክልሎች ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ አማራ እና አፋር ክልሎች ናቸው፡፡ በእነዚህ ክልሎች ሥር የሚከተሉት ቀጠናዎች የሰበካው ቀጠናዎች ሆነው ተጠቃልለዋል፣ እነዚህም መተከል፣ ሰሜን ጐንደር፣ ደቡብ ጐንደር፣ ምሥራቅ እና ምዕራብ ጐጃም፣ አገው እና አዊ ዞን፣ ዋግምራ፣ ሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሚያ ቀጠና አንድ፣ አራት እና አምስት ናቸው፡፡ በዚህ መሠረት ሥርዐቱ እንዲፈፀም እና ሰነዶቹም ወደ ቅድስት መንበር መዝገብ ቤት እንዲላኩ ይህ አዋጅ ያዝዛል፡፡ በዚህ አዋጅ ያወጣናቸው መመርያዎች በሙሉ ተፈፃሚ እንዲሆኑ ወደፊትም ተጠብቀው እንዲቀጥሉ ወስነናል፡፡ የጌታ ዓመት ተብሎ በሚጠራው በ2ዐ15 ዓ.ም በጵጵስናዬ ሁለተኛ ዓመት ጥር ዘጠኝ ቀን በሮም ቅድስት መንበር ተሰጠ፡፡

Translate »