Current News from PACO

በባህር ዳር ደሴ ካቶሊካዊ ሰበካ ሲመተ ዲቁና ተሰጠ!

እነርሱ በእውነት ቅዱሳን እንዲሆኑ እኔ ራሴን ስለ እነርሱ ቅዱስ አደርጋለሁ፡፡ ዮሐ 17፡19

ሚያዝያ 14 ቀን 2009 ዓ.ም በደብረ ማርቆስ ቅዱስ ዮሴፍ ቁምስና ንፍቀ ዲያቆን ደሳለኝ (ወልደገብርኤል) ሃይሌ ሚኑታ ከብፁዕ አባታችን አቡነ ልሳነክርስቶስ ማቴዎስ የባሕርዳር-ደሴ ሀገረ ስብከት ጳጳስ እጅ ማዕረገ ዲቁና ተቀብለዋል፡፡ በዕለቱ መስዋዕተ ቅዳሴውን የመሩት የባሕርዳር-ደሴ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ብፁዕ አባታችን አቡነ ልሳነክርስቶስ ማቴዎስ ሲሆኑ እንኳን ደህና መጣችሁ ካሉ በኃላ እግዚአብሄር ሰራት አበጃ ብለን ለምንደሰትባት ቀን እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል፡፡ ብፁዕነታቸው በስብከተ ወንጌል ባሰሙት መልዕክት እግዚአብሄር የሰራት ቀን ይህች ናት ሐሴትም እናድርግባት በእርሷም ደስ ይበለን (መዝ 118፡24) በማለት ነው የጀመሩት፡፡

የሚስጢር አዋቂ ና የሚስጢር አገልጋይ ከጉያቸው በመውጣት ለቤተክርስቲያ በመሰጠቱ ለቤተሰቦቹም ታላቅ ደስታ እንደሆነ በመግለፅ ይህም ለገሀረስብከታችን የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ዲያቆን እንደሆነ ገልፀው ይህንን ያደረገውን እግዚአብሄርንም አመስግነዋል፡፡ ብፁዕነታቸው አያይዘውም የሜክስካዊያ ዲያቆን ሪካዶ ማርቲንዝ ከሶስት ወር በፊት በጣሊያን ሀገር የሀገረስብከታችን የመጀመሪያ ዲያቆን መበሆን ሲመተ ዲቁናመቀበሉን በቦታው ለነበሩት ምዕመናን ካሳወቁ በኋላ ይህ እግዚአብሄር ለሀገረስብከታችን ከሚያደረግልን ታላላቅ ቅዱስ ስጦታዎች አንዱ ነው ብለዋል ዛሬ እኛ ብቻ ሳንሆን በዓለም ያለች ቤተክርስቲያንም ትደሰታለችበማለት ምን ያህል ታላቅ ደስታ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

ለዚህም ነው ቅዱሳን የሆኑ ካህናት፣ ቅዱሳና የሆኑ ደናግላን፣ ቅዱሳን የሆኑ ዲያቆናት እንዲሁም ቅዱሳን የሆኑ ምዕመናን ለቤተክርስቲያን በጣም አስፈላጊ ስለሆኑ ወደ እግዚአብሄር መፀለይ ይገባናልብለዋል፡፡ የዛሬ ወንጌልም እንደሚለን መከሩ ብዙ ነው የመከሩ ሰራተኞች ግን ጥቅቶች ናቸው ፡፡ በሰማይ ያለው አባታችሁ ቅዱስ እንደሆነ እናንተም ቅዱሳን ሁኑ እንደማን ሲባል እንደ እግዚአብሄርእንደሱ ለመሆን ይበዛብናል እንዳንል እሱ እኛን ለመሆን ካልሰነፈ እኛ እሱን ለመሆን ለምን እንቸገራለን? እሱ ሊያግዘን ዝግጁ ነው፡፡ የአቅም ጉዳይ አይደለም፣ የችሎታ ጉዳይ አይደለም የፍላጎት ጉዳይ ብቻ ነው በማለት ስብከታቸውን አጠቃለዋል ፡፡

Translate »