What we are working now

በባህር ዳር ደሴ ካቶሊካዊ ሰበካ ሲመተ ዲቁና ተሰጠ!

እነርሱ በእውነት ቅዱሳን እንዲሆኑ እኔ ራሴን ስለ እነርሱ ቅዱስ አደርጋለሁ፡፡ ዮሐ 17፡19

ሚያዝያ 14 ቀን 2009 ዓ.ም በደብረ ማርቆስ ቅዱስ ዮሴፍ ቁምስና ንፍቀ ዲያቆን ደሳለኝ (ወልደገብርኤል) ሃይሌ ሚኑታ ከብፁዕ አባታችን አቡነ ልሳነክርስቶስ ማቴዎስ የባሕርዳር-ደሴ ሀገረ ስብከት ጳጳስ እጅ ማዕረገ ዲቁና ተቀብለዋል፡፡ በዕለቱ መስዋዕተ ቅዳሴውን የመሩት የባሕርዳር-ደሴ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ብፁዕ አባታችን አቡነ ልሳነክርስቶስ ማቴዎስ ሲሆኑ እንኳን ደህና መጣችሁ ካሉ በኃላ እግዚአብሄር ሰራት አበጃ ብለን ለምንደሰትባት ቀን እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል፡፡ ብፁዕነታቸው በስብከተ ወንጌል ባሰሙት መልዕክት እግዚአብሄር የሰራት ቀን ይህች ናት ሐሴትም እናድርግባት በእርሷም ደስ ይበለን (መዝ 118፡24) በማለት ነው የጀመሩት፡፡

የሚስጢር አዋቂ ና የሚስጢር አገልጋይ ከጉያቸው በመውጣት ለቤተክርስቲያ በመሰጠቱ ለቤተሰቦቹም ታላቅ ደስታ እንደሆነ በመግለፅ ይህም ለገሀረስብከታችን የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ዲያቆን እንደሆነ ገልፀው ይህንን ያደረገውን እግዚአብሄርንም አመስግነዋል፡፡ ብፁዕነታቸው አያይዘውም የሜክስካዊያ ዲያቆን ሪካዶ ማርቲንዝ ከሶስት ወር በፊት በጣሊያን ሀገር የሀገረስብከታችን የመጀመሪያ ዲያቆን መበሆን ሲመተ ዲቁናመቀበሉን በቦታው ለነበሩት ምዕመናን ካሳወቁ በኋላ ይህ እግዚአብሄር ለሀገረስብከታችን ከሚያደረግልን ታላላቅ ቅዱስ ስጦታዎች አንዱ ነው ብለዋል ዛሬ እኛ ብቻ ሳንሆን በዓለም ያለች ቤተክርስቲያንም ትደሰታለችበማለት ምን ያህል ታላቅ ደስታ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

ለዚህም ነው ቅዱሳን የሆኑ ካህናት፣ ቅዱሳና የሆኑ ደናግላን፣ ቅዱሳን የሆኑ ዲያቆናት እንዲሁም ቅዱሳን የሆኑ ምዕመናን ለቤተክርስቲያን በጣም አስፈላጊ ስለሆኑ ወደ እግዚአብሄር መፀለይ ይገባናልብለዋል፡፡ የዛሬ ወንጌልም እንደሚለን መከሩ ብዙ ነው የመከሩ ሰራተኞች ግን ጥቅቶች ናቸው ፡፡ በሰማይ ያለው አባታችሁ ቅዱስ እንደሆነ እናንተም ቅዱሳን ሁኑ እንደማን ሲባል እንደ እግዚአብሄርእንደሱ ለመሆን ይበዛብናል እንዳንል እሱ እኛን ለመሆን ካልሰነፈ እኛ እሱን ለመሆን ለምን እንቸገራለን? እሱ ሊያግዘን ዝግጁ ነው፡፡ የአቅም ጉዳይ አይደለም፣ የችሎታ ጉዳይ አይደለም የፍላጎት ጉዳይ ብቻ ነው በማለት ስብከታቸውን አጠቃለዋል ፡፡

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በግልገልበለስ በካቶሊካዊት  ቤተክርስቲያ የቅድስት ቤተሰብ በዓል በድምቀት ተከበረ

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በመተከል ዞን በማንዱራ ወረዳ ግልገል በለስ ከተማ ካቶሊካዊት  ቅድስት ማሪያም የክርስቴያኖች እናት ቁምስና እና ዙሪያ ያሉ ካቶሊክ ጽሎት ቤቶች የገና በዓል አስመልክቶ ከዋዜማ ታህሳስ ቀን 28 ጀምሮ እስከ 30/04/2009 ዓ.ም ለ3 ተከታታይ ቀናት በደማቅ ሁኔታ ተከበሯል፡፡

 

ይህ እንዲህ እንደለ በየዓመቱ የሚከበረው የካቶሊክ ናዝሬት የቅድስት ቤተሰብ በዓል መነሻ በማደረግ ከቅዳሴ በፊት በቀን 30/04/2009 ዓ.ም ያለው ቤተስቦች ለበርካታ ዓመታት ሥርዓተ ተክሊል ትምህርት በሚገባ ተከታተለው 9 ቤተሰቦች ምስጢረ ተክሊል የወሰዱ ሲሆን 11 የተጋቢዎች ህጻናት ደግሞ ምስጢረ ጥምቀት ከአባ እያቄም ሲልቫ እጅ እንዲወሰዱ ተደረገዋል፡፡ ይህ ምስጢረ ተክሊል ለ2ኛ ጊዜ ቤተክርስቴያኗ የሰጠች መሆኗ አባ እያቄም ገለፁ፡፡ በበዓሉ ተሳታፊ የሆኑ የግልገለ በለስ ፈራንቺስካዊያን ሲስተሮች፣ማህበር ኮምቦኒ አባቶች እና ተጋባዥ እንግዶች ምስጢረ ተክሊል ለተቀበሉት ቤተሰቦች የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ እና ደም አንድ መሆናችን አድናቆታቸውን በመገለጽ  የተለያዩ ሽልማቶች አዝጋጀቶ  አበረከቷላችዋል፡፡ በተላይ በካቶሊክዊት ቤተክርስቴያን የሚደረግ መንፈሳዊ ጋብቻ ለጉምዝ እና ለሌሎች ማህበረስብ ምርጥ ተሞክሮ የሚገለጽ ስለሆነ ከዚህ በፊት በተለያዩ መንገድ በጎጂ ልማደዊ ድርጊቶች ሰለባ የሆኑ ህጻናትና ሴቶች ችግር ተቀርፎ ዘላቂ መፍተሄ ይሰጣል የሚል አስተያያት ተቀበሎ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በጋራ መስራት እንዳለበት በትኩረት ወሰዷል፡፡

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮ ለካቶሊክ ቤተክርስቴያን ለቤተሰቦች ቅደም ብሎ ባስተላለፉት መልዕክት ‹‹የፍቅር ደሰታ ልምምድ በቤተሰብ መሆኑን ለቤተክርስቴያንም ጨምር  ደሰታ የሚስጥ ነው›› ይህን የተቀደሰ ሃሳብ በጉምዝ ማህበረስብ ዘንድ የቤተክርስቴያኗን አስተምሮ ተግባራዊ ማደረግ ይጠበቀበታል፡፡ በመጨረሻ በዓሉን በተለያዩ ሙዝሙሮች እና ዝግጀቶች ተከበሮ በሠላማዊ መንገድ ተጠናቀቅዋል፡፡

በጎንደር አስትሪዮ ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በድምቀት ተከበረ

በጥር 21፤2009ዓ.ም በጎንደር ካቶሊክ ቤተክርስቲያ በደብረ ሰላም አስትሪዮ ማርያም ቁምስና ዓመታዊ ክብረ በዓል በደማቅ ሁኔታ ተከበረ፡፡ በበዓሉ ላይም የባህር ዳር ደሴ ሀገረስብከት ጳጳስ አቡኔ ልሳነ ክርስቶስ ማቴዎስ ቃለ ወንጌልን ያሰሙ ሲሆን የእሳቸው መገኘት ለበዓሉ ትልቅ ድምቀት ነው በማለት የቁምስናው ቆሞስ ክቡር አባ ደሳለኝ ዮሴፍ ተናግረዋል፡፡ ብፁነታቸውም በቃለ ወንጌሉ ላይም ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ድንግል ማርያም የዓለሙ ሁሉ መዳን ምክንያት ስለሆነች ለአማላጅነቷ ትልቅ ቦታ ይሰጣል። አማላጅነት በእግዚአብሔር ዘንድ ለተከበሩ በፈቃዱ ለሚሄዱ የሚሰጥ የክብራቸው መገለጫ የሆነ የቅድስና ደረጃ ነው ። ድንግል ማርያም አማላጃችን እንድትሆን ከሁሉ በላይ የፈቀደ እግዚአብሔር ነው ።

እመቤታችን ድንግል ማርያም በቃና ሰርግ ቤት ተገኝታ የወይን ጠጅ የላቸውም ብላ እንዳማለደች( ዮሐ 2፡1—11) በእኛም ሕይወት የጎደለብንን ነገር እግዚአብሔር እንዲሞላልን ዘወትር ትጠይቃለች። መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል መላእክትን በመወከል ኤልሳቤጥ ደግሞ የሰው ልጆችን በመወከል ጸጋን የተሞላብሽ በማለት ለእመቤታችን ምስጋና አቅርበዋል። እመቤታችንም በሰጠችው የሃይማኖት ምስክርነት “ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል” ሉቃ 1፡49 ብላለች። ይህን የተናገረችው ለእርሷ ምስጋና ማቅረብ የእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑን ሰዎች ተረድተው ፡ : በዚሁ ፈቃድ መሠረት እንዲመሩ ነው ። ድንግል ማርያም እንድትመሰገን እግዚአብሔር ከፈቀደ ሰዎቸ በተቃዉሞ ቢነሱ በመጨረሻው ቀን ተጠያቂ ያደርጋቸዋል ምክንያቱም “በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።በዚያ ቀን ብዙዎች። ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል።የዚያን ጊዜም ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።” ማቴ 7 ፡21—23. ብሎ ጌታችን ተናግሯል ። እኛ ግን እንደተማርነው ድንግል ማርያምን ዘወትር እናመሰግናታለን ፤ ይህንን በማድረጋችን የበለጠ ወደ እግዚአብሔር እንቀርባለን እንጂ አንርቅም።

Ethiopia’s Eparchy of Bahirdar-Dessie Baptises 300 Catechumens

Banush New Cathecucmens Baptisim
Banush New Cathecucmens Baptisim

The Ethiopian Catholic Eparchy of Bahir dar-Dessie, baptised 300 Catechumens among the people of Gumuz, in Banshagul Gumuz Regional State, this week, on the Feast of the Miraculous Medal. Many of the newly baptized converted from local traditional religions to Catholicism. Most of the Catechumens are from a place known as Banush, a very remote area located 600 km from the capital, Addis Ababa.

At the request of the people’s request, Bishop Lesanu-Christos, the Eparch of  Bahirdar-Dessie, blessed and erected a cross and a bell on the future site of a Church. Another cross was placed at the community’s cemetery as a sign of a new Christian community. The Bishop with the help of 6 priests then baptised the 300 new Christians who comprised old, young, men and women as well as some infants.

Banush 300 New Cathecumens Baptism
Banush 300 New Cathecumens Baptism

In his homily, Bishop Lesanu-Christos said that the day was a joyous one for the Church. “God is Great, and God is a Father to all of us; we say the Our Father Prayer here and throughout the world and this proves that we are all children of one God who he created everyone equally and with the same human dignity. Today when you receive this great Sacrament of Baptism you become sons and daughters of God, people of God and members of the Church, this brings great joy in heaven and great joy on earth for the entire Church,” said Bishop Lesanu-Christos congratulating the new followers of Christ.

The Bishop of Bahirdar-Dessie also noted that the community was evangelised by a local, young man named Takel. It was Takel who first brought the request of the village to the Church’s attention asking the Church authorities to bring the light of Christ to his community in the remote area of Banush. The Bishop stressed the importance of continued evangelization in the area saying there still many people who have not been as lucky as the Baptised Banush community.

Banush 300 new Cathecumens Baptism
Banush 300 new Cathecumens Baptism

“The testimony of one young believer and the diligent efforts of the pastoral agents of the Catholic Church have brought 300 more children of God home. However, there are still more of our brothers and sisters who have not yet received the Good News of the Lord, and with God’s Grace we shall continue to shine the light of Our Lord and spread the Good News,” the Bishop said.

The newly baptised Christians celebrated by wearing and lighting candles as a sign of the light of Christ shining in them. They sang in the local language: “We know what we trust in.” The ceremony was attended by families of the baptised, the clergy, religious men and women, Catechists and the faithful from different parishes of Diocese.

Banush 300 new Cathecumens Baptism
Banush 300 new Cathecumens Baptism

The Eparch of Bahirdar-Dessie is the youngest Ecclesiastical Jurisdiction of the Ethiopian Catholic Church. Currently, there are more than 500 Catechumens in neighbouring villages who are eagerly waiting to be baptised. The Catholic Church first went to the Gumuz people 15 years ago. Three Comboni sisters planted the first seed of faith: Sr. Jamilety, Tilda, and Bertila. The sisters first arrived in Mandura district and begun the work of evangelization.

Translate »